ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ስራዎች የሚለኩት በኒያ (በሀሳብ) ብቻ ነው። ሰውየው የሚያገኘው ያሰበውን ነው። ስደ...
ሶሒሕ ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሁሉም ስራዎች ግምት የሚሰጣቸው በኒያ እንደሆነ አብራሩ። ይህ ብይን በአምልኳዊም ጉዳይ ሆነ ከሰው ጋር ባሉ መስተጋብሮች ሁሉንም ስራዎች የሚያጠቃልል ነው። በስራው የሆነን ጥቅም ያሰበ ሰው ከዛች ጥቅም በስተቀ...
ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹በዚህ በመመሪያችን ውስጥ ከርሱ (ከትእ...
ሶሒሕ ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር የፈጠረ ወይም ቁርአናዊና ሐዲሣዊ ማስረጃ ያልጠቆሙትን ስራ የሰራ ሰው በባለቤቱ ላይ ተመላሽ እንደሚሆንና አላህ ዘንድም ተቀባይነት እንደማይኖረው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።
ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ ከዕለታት አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ሳለን ድንገት ልብሱ እጅግ በጣም ነጭ የሆነ፤ ፀጉሩ ደግሞ እጅግ በጣም ጥቁር...
ሶሒሕ ነው።
ሙስሊም ዘግበውታል።

ዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከዕለታት አንድ ቀን ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በሶሐቦች መካከል አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በማይታወቅ ሰው ተመስሎ እንደወጣ ይናገራሉ። ከዚህም ሰውዬ ባህሪ ልብሱ እጅግ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: «እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነ...
ሶሒሕ ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢስላምን አምስት አስተማማኝ ምሶሶዎች እንደተሸከሙት ቤት አድርገው መሰሉት። የተቀሩትን የኢስላም ጉዳዮች ደግሞ ቤቱን እንደሚያሟሉ ነገሮች ናቸው። ከእነዚህ ማእዘናት የመጀመሪያው: ሁ...
ሙዓዝ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ : ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኋላ ዑፈይር የሚባለው አህያ ላይ ተፈናጥጬ ሳለው "ሙዓዝ ሆይ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅ፤ ባሮችስ አላህ ዘንድ ያላቸ...
ሶሒሕ ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅና ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ አብራሩ። አላህ ባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ እሱን ብቻ ሊያመልኩና በሱ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ ነው። ባሮች በአላህ ላይ ያላቸ...

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሁሉም ስራዎች ግምት የሚሰጣቸው በኒያ እንደሆነ አብራሩ። ይህ ብይን በአምልኳዊም ጉዳይ ሆነ ከሰው ጋር ባሉ መስተጋብሮች ሁሉንም ስራዎች የሚያጠቃልል ነው። በስራው የሆነን ጥቅም ያሰበ ሰው ከዛች ጥቅም በስተቀር ሌላ አያገኝም። ምንዳም የለውም። በስራው ወደ አላህ መቃረብን ያሰበ ሰው ደግሞ እንደ መብላትና መጠጣት የመሰሉ ተለምዷዊ ስራ ቢሆንም እንኳ ሰርቶ በስራው ምንዳና አጅርን ያገኛል። ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስራዎች በውጫዊ ይዘታቸው ሲታዩ ተመሳሳይ ከመሆናቸውም ጋር ኒያ በስራዎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ ለማብራራት ምሳሌ ጠቀሱ። በስደቱና ሀገሩን በመተዉ የአላህን ውዴታ ማግኘትን ያሰበ ስደቱ ሸሪዐዊና ተቀባይነት ያለው ስደት ነው። ኒያው እውነተኛ ስለሆነም ይመነዳበታል። በስደቱ ግን እንደ ገንዘብ፣ ክብር፣ ንግድና ሚስት የመሳሰሉ ዓለማዊ ጥቅም የፈለገ ሰው ከስደቱ ይህችን ያሰባትን ጥቅም በስተቀር ሌላ አያገኝም። ከምንዳና አጅርም ምንም እጣ ፈንታ እንደሌለው ገለፁ።
Hadeeth details

በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር የፈጠረ ወይም ቁርአናዊና ሐዲሣዊ ማስረጃ ያልጠቆሙትን ስራ የሰራ ሰው በባለቤቱ ላይ ተመላሽ እንደሚሆንና አላህ ዘንድም ተቀባይነት እንደማይኖረው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።
Hadeeth details

ዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከዕለታት አንድ ቀን ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በሶሐቦች መካከል አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በማይታወቅ ሰው ተመስሎ እንደወጣ ይናገራሉ። ከዚህም ሰውዬ ባህሪ ልብሱ እጅግ የነጣ፣ ፀጉሩም እጅግ የጠቆረ ነበር። በሱ ላይም ድካም፣ አቧራ፣ የፀጉር መንጨባረርና የልብስ መቆሸሽ የመሰሉ የጉዞ ምልክት አይታይበትም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ተቀምጠው ከነበሩ ታዳሚዎች መካከልም አንድም ሰው አላወቀውም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፊት እንደተማሪ አቀማመጥ ተቀመጠ። ስለ ኢስላምም ጠየቃቸው። እሳቸውም በሁለቱ የምስክር ቃላት ማረጋገጥን፣ አምስቱ ሶላቶች ላይ መጠባበቅን፣ ለሚገባው ሰው ዘካ መስጠትን፣ የረመዷን ወር መፆምን፣ በቻለ ላይ ግዴታ የሆነውን ሐጅ መፈፀምን ያካተተውን እነዚህን ማዕዘናት በመጥቀስ መለሱለት። ጠያቂውም "እውነት አልክ!" አለ። ሶሐቦችም ከላይ ሲታይ አጠያየቁ አለማወቁን የሚጠቁም፤ ከዛ ደግሞ ትክክለኛ መልስ እንደተመለሰለት ማረጋገጡን በማስተዋላቸው ግራ ተጋቡ። ከዚያም ስለ ኢማን ጠየቃቸው። እሳቸውም እነዚህን ስድስት ማዕዘናት ማመንን የሰበሰበ መልስ መለሱለት። እነሱም:-አላህ በመኖሩ፣ በባህሪያቶቹ፣ መፍጠርን በመሰሉ ድርጊቶቹና በአምልኮም ብቸኛ መሆኑን ማመን፤ አላህ ከብርሃን የፈጠራቸው መላእክቶች የተከበሩ ባሮቹ መሆናቸውን፣ አላህን የማያምፁና በትእዛዙ የሚተገብሩ መሆናቸውን ማመን፤ እንደ ቁርኣን፣ ተውራት፣ ኢንጂልና ሌሎችም ከአላህ ዘንድ በመልክተኞች ላይ በወረዱ መጽሐፍት ማመን፤ የአላህን ሃይማኖት የሚያደርሱ በሆኑ መልክተኞች ማመን ከነሱም መካከል ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳ፣ ዒሳና የመጨረሻቸው የሆኑት ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂም ወሰለምና ሌሎችም ነቢያቶችና መልክተኞች ይጠቀሳሉ። በመጨረሻው ቀን ማመን፤ እዚህ ምውስጥም ከሞት በኋላ ያሉ በቀብርና በበርዘኽ ህይወት እንዲሁም የሰው ልጅ ከሞት በኋላ የሚቀሰቀስና የሚተሳሰብ መመለሻውም ወይ ወደ ጀነት ወይ ወደ እሳት መሆኑን ማመንንም ያካትታል። አላህ በቀደመ ዕውቀቱ መሰረት፣ ጥበቡ ባስፈረደው መልኩ በፍላጎቱ መሰረት ነገሮችን እንደወሰነና በጽሑፍም እንዳሰፈረ ማመን፤ ምድር ላይ የሚከሰቱትም በወሰናትና በፈጠራት ልክ መሆኑንም ማመን ነው። ከዚያም ስለ ኢሕሳን (ስራን ማሳመር) ጠየቃቸው። ኢሕሳን ማለት ልክ አላህን እያዩ እንደሆነ እያሰቡ አላህን መገዛት ነው። እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ባይረጋገጥለት (ባይችል) እንኳ ልክ አላህ እርሱን እያየው እንደሆነ በማሰብ አላህን መገዛት ነው። የመጀመሪያው: የ "ሙሻሀዳህ" (አሏህን እያየህ እንደሆነ እያሰብክ የምታመልክበት) ደረጃ ነው እሱም የላቀ ደረጃ ነው። ሁለተኛው ደግሞ የ "ሙራቀባህ" (አሏህ እያየኝ ነው በሚል ሃሳብ የምታመልክበት) ደረጃ ነው። ከዚያም ሰዓቲቱ መቼ እንደሆነች ጠየቃቸው። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰዓቲቱ መከሰቻ ጊዜ አላህ በእውቀቱ ብቸኛ ከሆነበት ጉዳይ አንዱ በመሆኑ ተጠያቂውም ይሁን ጠያቂው ከፍጥረቱ መካከልም አንድም እንደማያውቀው ገለፁ። ከዚያም ስለ ሰዓቲቱ ምልክቶች ጠየቃቸው። ከምልክቶቿ መካከል የጭን ገረዶችና ልጆቻቸው እንደሚበዙ ወይም የልጆች የእናቶቻቸውን ሐቅ አለመወጣታቸው እንደሚበዛ ይህም ከእናቶቻቸው ጋር ያላቸው መስተጋብር ልክ ከባሪያ ጋር እንዳላቸው አይነት መስተጋብር እንደሚሆን፤ ለበግ እረኞችና ለድሆች በመጨረሻው ዘመን ዱንያ ተዘርግታላቸው በህንፃ ውበትና አሰራር እንደሚፎካከሩ ገለፁ። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠያቂው ጂብሪል እንደነበረና የመጣውም ይህንኑ ቀጥተኛ እምነት ለሶሐቦች ሊያስተምር እንደሆነ ተናገሩ።
Hadeeth details

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢስላምን አምስት አስተማማኝ ምሶሶዎች እንደተሸከሙት ቤት አድርገው መሰሉት። የተቀሩትን የኢስላም ጉዳዮች ደግሞ ቤቱን እንደሚያሟሉ ነገሮች ናቸው። ከእነዚህ ማእዘናት የመጀመሪያው: ሁለቱ የምስክርነት ቃላት ናቸው። እነርሱም: ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነው። እነዚህ ሁለቱ የምስክርነት ቃላት እንደ አንድ ማእዘን ናቸው። አንዱ ከሌላኛው ተለይቶ የሚታይ አይደለምና። የአላህን ብቸኛ መሆንና ከርሱ ውጪ ያለውን ትቶ በብቸኝነት ለአምልኮ የተገባው እርሱ ብቻ መሆኑን በማመን፣ የሚያስፈርዱትን በመተግበር፣ በሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልዕክተኝነታቸውን በማመንና እርሳቸውን በመከተል አንድ ባሪያ እነዚህን ሁለት የምስክርነት ቃላት ይናገራል። ሁለተኛው ማእዘን: በቀንና በምሽት የሚሰገዱ የሆኑት የፈጅር፣ የዙህር፣ የዐስር፣ የመጝሪብ እና የዒሻእ ሶላቶችን መስፈርቶቹን፣ ማእዘናቶቹንና ግዴታዎቹን ጠብቆ ማቋቋም ነው። ሶስተኛው ማእዘን: ግዴታ የሆነውን ዘካ ማውጣት ነው። ይህም ገንዘቡ በሸሪዓ የተወሰነውን ያህል መጠን የደረሰ ባለገንዘብ በሙሉ፤ ለሚገባው አካል ሊሰጥ ግዴታ የተደረገበት ገንዘባዊ አምልኮ ነው። አራተኛው ማእዘን: ሐጅ ነው። እርሱም: አምልኳዊ በሆነ መልኩ የሐጅ ተግባራትን ለመፈፀም መካን ማሰብ ነው። አምስተኛው ማእዘን: ረመዷንን መፆም ነው። እርሱም: አላህን በማምለክ ኒያ ጎህ ከወጣችበት ሰአት ጀምሮ ፀሀይ እስከምትጠልቅ ድረስ ከመብላት፣ ከመጠጣትና ሌሎችም ፆምን ከሚያስፈጥሩ ነገሮች መቆጠብ ማለት ነው።
Hadeeth details

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅና ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ አብራሩ። አላህ ባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ እሱን ብቻ ሊያመልኩና በሱ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ ነው። ባሮች በአላህ ላይ ያላቸው ሀቅ ደግሞ እነዚያ በሱ ላይ አንዳችንም ሳያጋሩ በብቸኝነት ያመለኩትን ላይቀጣ ነው። ቀጥሎ ሙዓዝ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሰዎች በደስታ እንዲበሰሩ በዚህ የላቀ የአላህ ትሩፋት ላበስራቸውን?" አለ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሷ ላይ መደገፋቸውን ፈርተው እንዳያበስራቸው ከለከሉት።
Hadeeth details

ሙዓዝ ቢን ጀበል -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መጋጓዣ ኋላ ተፈናጦ ሳለ እሳቸው "ሙዓዝ ሆይ!" በማለት ጠሩት። ለርሱ የሚነግሩት ነገር አንገብጋቢ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠትም ጥሪያቸውን ሶስት ጊዜ ደጋገሙት። ሙዓዝም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- በነዚህ ጥሪዎች ሁሉ "ለበይከ ያረሱለሏህ ወሰዕደይክ" ማለትም የአላህ መልክተኛ ሆይ!ደጋግሜ በደስታ አቤት ብያለሁ። እያለ ይመልስ ነበር። ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ሳይዋሽ በእውነተኛ ልቡ የሚመሰክር ሆኖ በዚህ ሁኔታው ላይ ከሞተ አላህ እሳትን በርሱ ላይ እርም እንደሚያደርግ ነገሩት። ሙዓዝም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ሰዎች እንዲደሰቱና በመልካም እንዲበሰሩ ልንገራቸውን? በማለት ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠየቀ። ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚህች ንግግር ላይ በመደገፍ ስራዎቻቸው እንዳታንስ ፈሩ። ሙዓዝም እውቀትን የመሸሸግ ወንጀል ውስጥ መውደቅን በመፍራት ከመሞታቸው በፊት ካልሆነ በቀር ከዛ በፊት ይህችን ሐዲሥ ለአንድም አልተናገረም።
Hadeeth details

በምላሱ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም ያለና የመሰከረ ሰው ፤ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደና ከኢስላም ውጪ ካሉ ሁሉ እምነቶች የጠራ ሰው በሙስሊሞች ላይ ገንዘቡና ደሙ እርም ይሆናል። እኛ ውጫዊ ከሆኑ ስራዎቹ በስተቀር መፈላፈል አይፈቀድልንም። በኢስላማዊ ህግጋት ይህንን የሚያስገድድ አስገዳጅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ገንዘቡም እንደማይነጠቅ ደሙም እንደማይፈስ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። የትንሳኤ ቀን ሂሳቡን በበላይነት የሚመራው አሏህ ነው። እውነቱን ከሆነ ይመነዳዋል። ሙናፊቅ ከሆነ ደግሞ ይቀጣዋል።
Hadeeth details

አንድ ሰውዬ ነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጀነት መግባትን ስለሚያስወስን እና እሳት መግባትን ስለሚያወስን ሁለት ነገሮች ጠቃቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን፦ ጀነትን የሚያስወስነው ነገር ሰውዬው አላህን በብቸኝነት እያመለከ በሱ አንዳችንም ሳያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት። እሳትን የሚያስወስነው ነገር ደግሞ ሰውዬው ለአላህ በተመላኪነቱ ወይም በጌትነቱ ወይም በስሞቹና ባህሪያቶቹ መሳይ እና አቻ በማድረግ በአላህ ላይ አንዳችን ነገር እያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት።
Hadeeth details

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ ውጪ ያለን አካል መጣራትና ከአላህ ውጪ ካለ አካል እርዳታ መፈለግን የመሰለ ለአላህ ሊደረግ ግዴታ የሆነን አንዳች ነገር ለሌላ እየሰጠ የሞተ ሰው የእሳት ባለቤት መሆኑን ነገሩን። ኢብኑ መስዑድም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በአላህ አንዳችን ሳያጋራ የሞተ ሰው መመለሻው ወደ ጀነት ነው የሚለውን ጨመሩ።
Hadeeth details

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙዐዝ ቢን ጀበልን - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ወደ አላህ መንገድ ተጣሪና አስተማሪ በማድረግ ወደ የመን በላኩበት ወቅት ከክርስቲያን የሆኑ ህዝቦችን ስለሚጋፈጥ እነርሱን በተመለከተ ዝግጁ እንዲሆን አሳሰቡት። ቀጥለውም ዳዕዋውን እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ነጥብ እንዲጀምር ነገሩት። መጀመርያ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" ብለው በአሏህ አንድነትና በሙሐመድ መልዕክተኝነት በመመስከር እምነታቸውን እንዲያስተካክሉ ጥሪ እንዲያደርግ፤ ምክንያቱም ወደ እስልምና የሚገቡት በዚህ የምስክርነት ቃል ስለሆነ ነው። ይህንንም ተግባራዊ ካደረጉ ሶላትን እንዲሰግዱ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ምክንያቱም ከተውሒድ በኋላ ትልቁ ግዴታ ይህ በመሆኑ ነው። ሶላትንም ካስተካከሉ በኋላ ከመካከላቸው ያሉት ባለ ፀጎች በመካከላቸው ላሉት ድሆች ከገንዘባቸው ዘካን እንዲያወጡ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለዘካ ብሎ ከውድ ንብረታቸው እንዳይወስድ አስጠነቀቁት። ምክንያቱም የመስጠት ግዴታቸው ከመካከለኛ ንብረታቸው ነውና። ከዚያም የተበዳይ ዱዓእ ተቀባይነቱ ከፍተኛ በመሆኑ ተበዳይ ዱዓእ እንዳያደርግበት ግፍን መጠንቀቅ እንዳለበት አሳሰቡት።
Hadeeth details

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን በምልጃቸው ከሰዎች ሁሉ የበለጠ እድለኛ የሚሆኑት "ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት" ማለትም ከአሏህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው እንደሌለ አምነው ከሽርክ ይሁን ከይዩልኝና ይስሙልኝም ጥርት ያሉት መሆናቸውን እየነገሩን ነው።
Hadeeth details

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢማን ተግባሮችን፣ እምነቶችንና ንግግሮችን የጠቀለለ ብዙ ክፍሎች እንዳሉት ተናገሩ። ከኢማን ክፍሎች ውስጥ በላጩና ከፍተኛው ትርጉሙን አውቆ ፣ የሚያስፈርደው በመተግበር "ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለት ነው። አላህ አንድና ብቸኛ አምላክ መሆኑንና ለአምልኮ የተገባ ብቸኛ አምላክ መሆኑን ከርሱ ውጪ ያለ ማንም እንደማይገባውም ማመን ነው። የኢማን ትንሹ ስራ ሰዎችን የሚያውክ የሆነን ነገር ሁሉ ከመንገዳቸው ላይ ማስወገድ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሓያእ (አይነ አፋርነት) የኢማን አንድ ክፍል መሆኑን ተናገሩ። ይህም መልካም ለመስራትና ፀያፍ ለመተው የሚያነሳሳ ባህሪ ነው።
Hadeeth details