The Encyclopedia of Ar-Rahman's Guests

Selected material for Pilgrims and Um-rah teaching it in languages of the world

Selected content

የዑምራ አፈፃፀምና ህግጋት አጠርያለ ማብራሪያ
የዑምራ አፈፃፀምና ህግጋት አጠርያለ ማብራሪያ
የሐጅ አፈፃፀም አጭር ማብራሪያ
የሐጅ አፈፃፀም አጭር ማብራሪያ
ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዱዓዎች
ከቁርኣንና ሐዲሥ የተውጣጡ ዱዓዎች
ተጨማሪ

Selected Quranic verses

ሐጅ (ጊዜያቱ) የታወቁ ወሮች ናቸው፡፡ በእነርሱም ውስጥ ሐጅን (እንዲሠራ) ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም፡፡ ከበጎም ሥራ የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል፡፡ ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው፡፡ የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ፡፡
[ሱረቱ አል-በቀራህ] • 197
በተቆጠሩ ቀኖችም ውስጥ (በሚና ጠጠሮችን ስትወረውሩ) አላህን አውሱ፡፡ በሁለት ቀኖችም ውስጥ (በመኼድ) የተቻኮለ ሰው በርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፡፡ የቆየም ሰው በርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፡፡ (ይህም) አላህን ለፈራ ሰው ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ እናንተ ወደርሱ የምትሰበሰቡ መኾናችሁንም ዕወቁ፡፡
[ሱረቱ አል-በቀራህ] • 203
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ የከብት፣ የበግና የፍየል እንስሳዎች ለእናንተ ተፈቀዱ፤ እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡
[ሱረቱ አል-ማኢዳህ] • 1
ካዕባን ጎብኝዎችን ማጠጣትንና የተከበረውን መስጊድ መሥራትን በአላህና በመጨረሻው ቀን እንዳመነና በአላህ መንገድ እንደታገለ ሰው (እምነትና ትግል) አደረጋችሁን አላህ ዘንድ አይተካከሉም፡፡ አላህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡
[ሱረቱ አት-ተውባህ] • 19
(አልነውም)፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና፡፡
[ሱረቱ አል-ሓጅ] • 27
ተጨማሪ

Selected prophetic hadiths

ከዒርባድ ቢን ሳሪያህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ቀን በመካከላችን ቆሙና በርሷ ምክንያት ልቦናዎች የራዱበት፣ ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰን ምክር መከሩን። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! የመከሩን ምክር የተሰናባች ምክር ሆኖብናልና ለእኛ የሚሰጡን አደራ አለን?' ተባሉ። እርሳቸውም ' አላህን በመፍራት፤ የሐበሻ ባሪያ እንኳ ቢሆን (መሪያችሁ) እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። ከኔ በኋላ ከባድ ልዩነትን ታያላችሁ፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።' አሏቸው።"
ሶሒሕ ነው።
አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ነበርን። የ14ኛዋን ሌሊት ጨረቃ ተመለከቱና እንዲህ አሉ: ' ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም። ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለው ሶላት ላይ አለመሸነፍን ከቻላቹ አድርጉት።' ቀጥሎ ይህንን አንቀፅ አነበቡ: '{ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው።}'"
ሶሒሕ ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ: ' 'ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ።'"
ሶሒሕ ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።"
ሶሒሕ ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከላቀውና ከተከበረው ጌታቸው ባስተላለፉት (ሐዲሥ) እንዲህ አሉ "አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ! " የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም አሁንም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ! የፈለግከውን ስራ በርግጥ ላንተ ምሬሃለሁ።"
ሶሒሕ ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ተጨማሪ